Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ በሶማሌ ክልል እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በሶማሌ ክልል እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ አደም ፋራህ “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ በጅግጅጋ ማዕከል ተገኝተው እየተሰጠ የሚገኘውን ስልጠና ተመልክተዋል።

ለፓርቲው ከፍተኛና የመካከለኛ አመራሮች እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና በሀገሪቱ 10 የስልጠና ማዕከላት እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን አቶ አደም ፋራህ በሁሉም የስልጠና ማዕከላት ተዘዋውረው በመቃኘት ላይ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

የዛሬው የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት የጅግጅጋ ጉብኝትም የዚሁ አካል መሆኑን ከብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመርሐ ግብሩ አቶ አደም ፋራህ ከሰልጣኝ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉና ለቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች መመሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.