Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቻይና ሲዥዋን ግዛት የምትገኘውን አረጓንዴዋን የቼንግዱ ከተማ ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ከሻንጋይ ጉብኝት በኋላ በቻይና ሲዥዋን ግዛት የምትገኘውን አረጓንዴዋን የቼንግዱ ከተማ ጎብኝተዋል።

ከቤጂንግ እና ሻንጋይ በመቀጠል ሶስተኛዋ ትልቅ ከተማ እንደመሆኗ ቼንግዱ ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ መንገድ ቁርኝት ፈጥራለች ነው የተባለው።

ከእነዚህም መካከል የቀጥታ የአየር ትራንስፖርት፣ የትምህርት፣የህክምና ትብብሮች እና የንግድ ግንኙነቶች ተጠቃሽ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)በቼንግዱ ቆይታቸው የግዙፍ ፓንዳ ማራቢያ የጥናት ማእከልን እና የቲያንፉ የግብርና ኤክስፖ ፓርክ መጎብኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

በሲዥዋን ግዛት የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ኃላፊ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) በተደረገላቸው የምሳ ግብዣ ወቅት÷ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል አቅም ባላቸው መስኮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.