Fana: At a Speed of Life!

የሰዓታት ተኩስ ማቆም ስምምነቱ በመክሸፉ እስራዔል የቦንብ ድብደባዋን ቀጥላለች ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔልና ሀማስ ለሰዓታት የተኩስ አቁም ላይ እንዲደርሱ የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሳይሳካ ቀርቶ እስራዔል ጋዛን መደብደብ መቀጠሏ ተሰማ፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ እስራዔል ጋዛ ላይ የምታደርሰውን ድብደባ እንድታቆም ለማሸማገል ጥረት ሲደረግ የቆየው የውጭ ፓስፖርት የያዙ ግለሰቦች ሀገሪቷን ለቀው እንዲወጡ ለማስቻል እና የዕርዳታ አቅርቦት ወደ ተከበበችው ፍልሥጤም ለማድረስ ነበር ተብሏል፡፡

ግጭቱ 10ኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን እስራዔል በዓየር የምታደርሰውን የቦንብ ጥቃት ይበልጥ አጠናክራ እንደቀጠለች እየተሰማ ነው፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃቱ በእስራዔል ምድር ጦር መታገዙም አይቀሬ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ በቀጣናው እየደረሰ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ መባባሱም ተጠቁሟል፡፡

እስራዔልን ያካተተው የግብፅ እና የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት በደቡብ ጋዛ ለሠዓታት ጦርነቱ እንዲቆም ሥምምነት ላይ መድረሱን ዘግሎብ ኤንድ ሜይል መዘገቡ ተገልጾ ነበር፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.