Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለእስራዔል ድጋፍ 2ኛውን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ላከች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ “ድዋይት ኤይዘን ሃወር” የተሰኘውን ሁለተኛውን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቧን ለእስራዔል ድጋፍ እንዲውል ወደ ሜዲትራኒያን ባሕር ላከች፡፡

ዋሽንግተን ቀደም ሲል “ጀራልድ ፎርድ” የተሰኘውን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ወደ ሜዲትራኒያን በመላክ ለእስራዔል ድጋፏ ማሳየቷ ይታወሳል፡፡

በሁለቱም ወገን ጦርነቱ ተባብሶ መቀጠሉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

እስራዔል ጋዛ ላይ በወሰደችው የዓየር ጥቃት እስካሁን ከ2 ሺህ 329 በላይ ፍልስጤማውያን ሕይወት አልፏል፡፡

ከ9 ሺህ 700 በላይ ፍልስጤማውያንም ቆስለዋል ነው የተባለው፡፡

በአንጻሩ ሃማስ በደቡባዊ እስራዔል ባደረሰው ጥቃት እስካሁን ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ÷ ከ3 ሺህ 400 በላይ በሚሆኑት ጉዳት አድርሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.