ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ የ25 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ሥምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ የ273 ሚሊየን የኖርዌይ ክሮነር ወይም ግምቱ (25 ሚሊየን ዶላር) የሚደርስ የድጋፍ ሥምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ሥምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቴዬን ክርስቴንሰን መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ያመላክታል፡፡
የድጋፍ ሥምምነቱ 148 ሚሊየን የኖርዌይ ክሮነርን የሚያካት ሲሆን ወደ ሥራ ሲገባ እየታየ በኖርዌይ መንግስት እንደሚለቀቅም ተመላክቷል፡፡
በኖርዌይ መንግስት የተለቀቀው ድጋፍ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የደን መጨፍጨፍ እና የደን መራቆትን ለመግታት ብሎም የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የሚውል ነው ተብሏል።
በተጨማሪም ድጋፉ ለሁለተኛው ዙር የኢንቨስትመንት መርሐ-ግብር የተያዘውን የገንዘብ ድጋፍ ያቀፈ መሆኑ ተመላክቷል፡፡