Fana: At a Speed of Life!

በአፍጋኒስታን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከተጎዱት አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕፃናት ናቸው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍጋኒስታን በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከተጎዱት አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕፃናት መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

የአፍጋኒስታን መሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ባሳለፍነው ቅዳሜ ዕለት ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ መከሰቱ የሚታወስ ነው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በሰጠው መረጃ÷በአደጋው ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሕክምና ተቋማት ከተወሰዱት ተጎጂዎች መካከል ሁለት ሦስተኛ ያኅሉ ሴቶችና ሕፃናት ናቸው፡፡

ቁጥሩ በመቶኛ ሲገለፅም ከ100 ተጎጂዎች መካከል 67 ያኅሉ ሴቶች አሊያም ደግሞ ሕፃናት ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡

ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያትም በሰዓቱ በሀገሪቷ ወንዶች ከቤት ውጭ የሚሆኑበት ሁኔታ ስለነበር መሆኑን የሬውተርስ መረጃ ጠቁሟል፡፡

በቅዳሜው የአፍጋኒስታን የመሬት መንቀጥቀ እስካሁን ከ2 ሺህ 400 በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን ሳያጡ እንዳልቀረ የታሊባን አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.