Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ከጀርመን የልማትና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በጀርመን የልማትና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የስደተኞችና ስደተኞች ተቀባይ ሀላፊ ታኒያ ፋብሪሲየስና ልኡካን ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በክልሉ በሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ጉዳይና በሰብአዊና የእርዳታ አቅርቦት ስራዎች ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም በሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.