ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ምቹ ከሆኑ 10 የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ ሆነች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ቢዝነስ ለመስራት ምቹ ከሆኑ 10 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ቀዳሚ መሆኗን የኦክስፎርድ ምጣኔ ሃብታዊ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
ቢዝነስ ኢንሳይደር “የአፍሪካ ምጣኔ ኃብታዊ ሪፖርትን” ዋቢ አድርጎ እንዳስነበበው÷አፍሪካ በዓለም ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ አህጉራት ውስጥ አንዷናት፡፡
የኦክስፎርድ ምጣኔ ኃብታዊ ሪፖርት በአፍሪካ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ምቹ የሆኑ10 የአፍሪካ ሀገራት በሚል ባወጣው ሪፖርትም ኢትዮጵያ ቀዳሚ መሆኗን ጠቅሷል፡፡
ሀገራቱ ያላቸው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ፣ ለዘርፍ ያላቸው ቀጣይ እቅድ፣ የተሟላ መሰረተ ልማት፣ በዘርፉ የሚገኘው ትርፍ እና ኪሳራ ፣ የጸጥታ ሁኔታ፣ የሚደረጉ ድጋፎች እና ሌሎች መስፈርቶችን በማወዳደሪያት ተጠቅሟል፡፡
በሪፖርቱ መሰረትም ኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ምቹ ከሆኑ10 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ቀዳሚ መሆን ችላለች፡፡
ከኢትዮጵያ በመቀጠልም ኮትዲቯርና ኡጋንዳ በቅደም ተከትል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን መያዛቸው ተመላክቷል፡፡