Fana: At a Speed of Life!

የመውሊድ በዓል ረቡዕ መስከረም 16 በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)1 ሺህ 498ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ ) ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2016ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገለፀ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በታላቁ አንዋር መስጊድ የሚከበረውን የመውሊድ በዓል አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡፡

በመግለጫው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ም/ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱል ከሪም ሼህ በድረዲን በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ የዘንድሮው መውሊድ በዓል አራተኛው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሙሌት በተካሄደበት ማግስት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ።

መውሊድን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት የተራቡትን በማብላት መሆን እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የታላቁ አንዋር መስጊድ ኢማም ሀጂ ጠሀ ሙሀመድ ሀሩን በበኩላቸው ÷መውሊድን ስናከብር አስተማሪያችን ፣አርዓያችን እና ፍቅርን ለዓለም ያስተማሩ የመጨረሻው ነብይ ነብዩ መሐመድ ሰ.ዐ.ወ ስራቸውን ለኡማው ለማስተላለፍ ለማስታወስ ነው ብለዋል።

በጋዜጣዊ መግለጫው በዓሉ የሰላምና የአንድነት እንዲሆንም መልክት ተላልፏል፡፡

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.