Fana: At a Speed of Life!

ማማ ዱይንግ ጉድ የሴቶችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከሁዋዌይ ጋር እየሰሩ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ ቀዳማዊት እመቤት ራቼል ሩቶ የሚመራው ‘ማማ ዱይንግ ጉድ’ የተባለው ድርጅት ሴቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማብቃት ከሁዋዌይ ጋር ጥምረት ፈጥሮ እየሰራ ነው።

ድርጅቱ ከ14 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኬንያ ሴቶች ማኅበራትን በዲጂታል ክኅሎት ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ከሁዋዌይ ኬንያ ጋር የመግባቢያ ሠነድ ተፈራርሟል፡፡

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የ”ማማ ዱይንግ ጉድ” ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ዶክተር ጆን ቹሞ ከሁዋዌይ ጋር የፈጠሩት ጥምረት ኬንያ እስከ ፈረንጆቹ 2030 ለማሳካት ከያዘችው ራዕይ ጋር የተጣጣመ ነው ብለዋል፡፡

ጥምረታቸው ሴቶችንም ተደራሽ በማድረግ ሁሉም ሰው ደስተኛ፣ የተሟላ እና የተለወጠ ሕይወት የሚኖርበትን ፍትሃዊ ማሕበረሰብ የመፍጠር ዓላማ ያነገበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሁዋዌይ ኬንያ ምክትል ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ስቲቨን ዣንግ በበኩላቸው፥ የኬንያ ሴቶችን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማገዝ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን አፍሪካ ቴክ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.