Fana: At a Speed of Life!

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ- ግብሮች እና የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 313 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

የዩኒቨሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አወል ሰዒድ (ዶ/ር ) በምረቃ ሥነ – ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ተመራቂዎቹ ከመጀመሪያ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ተመራቂዎቹ በተማሩበት መስክ ለሀገራቸው ዕድገት መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም አመላክተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ባሻገር በምርምርና ማሕበረሰብ አገልግሎት ላይ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቅድመና ድኅረ ምረቃ መርሐ- ግብሮች ያሠለጠናቸውን 1 ሺህ 475 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት÷ ተመራቂዎች በአብሮነት የመኖርና የመሥራት ባህልን በመጠቀም ሀገራቸውን በሚያሳድጉ ተግባራት ላይ በትጋት እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡

በከድር መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.