Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና አልጄሪያ መካከል የቀጥታ የአውሮፕላን በረራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና በአልጄሪያ መካከል የመጀመሪያው የቀጥታ በረራ ተደርጓል፡፡

የቀጥታ በረራውን በአልጀሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአልጀርስ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከአልጄሪያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዮሴፍ ቸርፋ እና ከሀገሪቱ አየር መንገድ ዳይሬክተር ጄኔራል ያስኔ ቤን ስሊማኔ ጋር ዛሬ አስጀምረውታል፡፡

በማስጀመሪያ በረራው አምባሳደር ነብያት ጌታቸውና በዮሴፍ ቸርፋ የተመራ የአልጄሪያ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ማድረጉን በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.