ከ300 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ተደመሰሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ300 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ሲደመሰሱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አባላቱ መቁሰላቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።
በሶማሊያ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ ሃይል ለመቀየር ተልዕኮ ወደ ሚፈፀምበት ቦታ በተንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ ጠላት ቀድሞ ባገኘው መረጃ መሠረት ደፈጣ ይዞ ጥቃት ለመሠንዘር የሞከረው አልሸባብ ባላሠበው መልኩ ክፉኛ መመታቱ ተገልጿል።
በተሳሳተ ስሌት የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ ቅይይር ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረው የአልሸባብ ሃይል ከ300 በላይ ታጣቂዎቹ ሲገደሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አባላቱም ቆስለዋል።
በሶማሊያ የሚገኘውን የሠላም አሥከባሪ ሀይል ለመቀየር የተንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ ሠራዊት የአልሸባብን ደፈጣ በማስወገድ፣ የጠመደውን ፈንጂና መሠናክል በማስወገድ ከተልዕኮው ቦታ ሁዱር መድረስ መቻሉ ተገልጿል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊቱ ምግብና ውሃ በማቅረብ ለሰራዊቱ የሰጠው ከፍተኛ ሞራል ህብረተሰቡ አልሸባብን የማይቀበል መሆኑን እንደሚያሳይ ተነግሯል።
የአልሸባብ ሃይል ሶስት ፈንጂ የጫኑ መኪናዎችንና 12 ፈንጂ የታጠቁ ታጣቂዎቹን እንዲሁም ከ1 ሺህ በላይ አባላቱን በደፈጣ ቢያሰልፍም የጥፋት ሃሳቡን ሳያሳካ መደምሰሱን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መረጃ አመላክቷል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!