Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከተመድ የአየር ንብረት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተመድ የአየር ንብረት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰን ጋር ተወያዩ።

 

ውይይቱ በኩባ ከሚካሄደው የቡድን 77 አባል ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን የተካሄደ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

 

በዚህ ወቅትም አቶ ደመቀ የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በኢትዮጵያ ስላለው የአየር ንብረት እና የልማት ጉዳዮችን በተመለከተ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

 

አያይዘውም ኢትዮጵያ ቀጠናዊ ውህደትን ለማሳደግ በምታደርገው ጥረት የኃይል ምንጮቿን ለማስፋት ማቀዷንም ገልጸውላቸዋል።

 

የተመድ የአየር ንብረት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰን በበኩላቸው የተመድ የአየር ንብረት ፕሮግራም በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

 

ኢትዮጵያ አራተኛውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት በማከናወኗም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.