ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው የቡና ሣምንት ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከኢንተር-አፍሪካ ቡና ድርጅት ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ሰሎሞን ሩታጌ ጋር ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ የካቲት 2024 በምታዘጋጀው የቡና ሣምንት ላይ መከሩ፡፡
ዐውደ-ርዕዩን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን፣ የኢንተር-አፍሪካ ቡና ድርጅት እንዲሁም አዲስ አበባ የሚገኘው ፋይን የአፍሪካ ቡና ማኅበር በትብብር እንደሚያዘጋጁት ተመላክቷል፡፡
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ቡና አምራቾች እና ሸማቾች በዐውደ ርዕዩ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል መባሉን የቡናና ሻይ ባለስልጣን መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ አውደ ርዕዩን በዓለምአቀፍ ደረጃ አዳዲስ የቡና ገበያ መዳረሻዎችን ለማፈላለግ እንደምትጠቀምበት ተጠቁሟል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!