Fana: At a Speed of Life!

ለመንገድ ደህንነት መረጋገጥ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተሽከርካሪ አደጋን ለመቀነስና ለመንገድ ደህንነት የተሻለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ትራፊክ ፖሊሶች፣ አሽከርካሪዎችና ተቋማት ሀገር አቀፍ የእውቅና መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ÷ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ባለፉት አራት ዓመታት በተሽከርካሪ አደጋ ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎችን መጠን የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም አሁንም ብዙ መስራት ይጠይቃል።

የአሽከርካሪዎች ህግና ስርአት አክብረው አለመስራት እና በቂ ስልጠና ሳይወስዱ ማሽከርከር ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥር ስራ አለመጠናከርና ክፍተቶች መታየታቸው የተሽከርካሪ አደጋን በሚፈለገው ደረጃ እንዳይቀንስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀማል አባሶ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ በተከናወነው ስራ ውጤት እየተመዘገበ ነው።

በ2010 ዓ.ም 936 ሺህ ተሽከርካሪ በነበረበት ወቅት 5 ሺህ 118 ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል ነው ያሉት።
በ2015 ዓ.ም የተሽከርካሪ ቁጥሩ ወደ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ከፍ ማለቱን ጠቁመው÷ በመኪና አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 577 መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአደጋ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች መጠን ለመቀነስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ ላይ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.