Fana: At a Speed of Life!

የዋጋ ንረት እንዲከሰት በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል- አቶ አወሉ አብዲ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መንገድ የዋጋ ንረት እንዲከሰት የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች እና ደላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ገለጹ፡፡

በአቶ አወሉ አብዲ የተመራ ልዑክ በክልሉ ከተሞች ለበዓል ፍጆታ የሚውሉ መሰረታዊ የገበያ አቅርቦትን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት አቶ አወሉ እንዳሉት÷ የክልሉን ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

በዚህም ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ተችሏል ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

የገበያ ንረትን ለማረጋጋትም መንግስት ለመሰረታዊ ፍጆታዎች የሚውሉ ምርቶችን በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እያቀረበ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.