Fana: At a Speed of Life!

ለሀሞት ጠጠር አጋላጭ ምክንያቶች ምንድናቸው?

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለምዶም የሐሞት ጠጠር የምንለው የሐሞት ፊኛ ውስጥ ጠጠር ሲከማች ነው።

ይህ ጠጠር ለምን እና እንዴት እንደሚፈጠር ሳይንሳዊ ድምዳሜ ላይ መድረስ ባይቻልም የተለያዩ መላምቶችን ግን መጥቀስ ተችሏል።

እነዚህም መላምቶች፣ ኮሊስትሮል በሐሞት ውስጥ መብዛት፣ ቢሉሩቢን በሐሞት ውስጥ መብዛት እና የሐሞት ፊኛ በውስጡ የሚገኘውን የሐሞት ፈሳሽ ወደ አንጀት መግፋት አለመቻል የሚሉትን እንደሚያጠቃልል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ለመሆኑ አንድን ሰው ለሐሞት ፊኛ ጠጠር ተጋላጭ ሊያደርጉት የሚችሉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

ጾታ (በአብዛኛው ሴቶች ተጋላጭ ናቸው)፣ዕድሜ ከ40 አመትና ከዚያ በላይ መሆን ፣የሰውነት ክብደት መጨመር፣ የሌሎች ተጓዳኝ በሽታ (እንደ ስኳር፣ ደም ግፊት) መኖር፣የተለያዩ መድሀኒቶች(የሚዋጥ የወሊድ መቆጣጠሪያ፣ ኮሊስትሮልን ለመቆጣጠር የሚወሰዱ መድሀኒቶች )እናቤተሰብ ውስጥ የሐሞት ጠጠር ያለበት ሰው መኖር ከብዙዎቹ ዋናዎቹ ናቸው።

የሐሞት ከረጢት ጠጠር ምን አይነት ምልክቶች አሉት?

አብዛኛውን ጊዜ ምንም አይነት ምልክት አያሳይም፤ ስለሆነም የሚታወቀው ለሌላ በሽታ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት ነው።

ምልክት ካሳየ ግን ዋነኛ የሚሆነው የሆድ ህመም ሲሆን ÷ህመሙም የመውጋት ስሜት እንደሚኖረው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሕክምናውም ምልክት ካላሳየ ቋሚ ክትትል ከማድረግ ውጪ ሌላ ህክምና የለውም፤ ምልክት ካሳየ ግን የቀዶ ሕክምና ብቸኛው መፍትሔ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.