Fana: At a Speed of Life!

ካሊክስ ኬሚካልስና ፋርማሲዩቲካልስ ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ካሊክስ ኬሚካልስ እና ፋርማሲዩቲካልስ የተሰኘው የህንድ ግዙፍ ኩባንያ በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

ኩባንያው በአለም አቀፍ ደረጃ 60 በመቶ የሚሆነውን የወባ እና የሳንባ ነቀርሳ መድሀኒት ግብዓቶች የሚያቀርብ ግዙፍ ድርጅት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኩባንያው ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር ስለኢንቨስትመንት እቅዱ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ኢንቨስትመንቱ በአፋጣኝ እውን እንዲሆን ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚደረግ አቶ አክሊሉ አረጋግጠዋል፡፡

የኩባንያው ተወካዮች በቆይታቸው የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን መጎብኘታቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.