Fana: At a Speed of Life!

ክልሉ ከ43 ሺህ ቶን በላይ ቅመማቅመም ለማዕከላዊ ገበያ አቅርቧል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት 43 ሺህ 141 ቶን ቅመማቅመም ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ቡና፣ ሻይ እና ቅመማቅመም ባለስልጣን  ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የቡና፣ ሻይና ቅመማቅማም ልማትና ጥበቃ ዘርፍ ኅላፊ አቶ በላይ ኮጁአብ እንደተናገሩት፤ በተጠናቀቀው በጀት አመት በ83 ሺህ 322 ሄክታር መሬት ላይ ቅመማቅመም ለምቷል።

ከዚህም 47 ሺህ 275 ቶን ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ 43 ሺህ 141ቶን የቅመማቅመም ምርት ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።

ይህም የዕቅዱን 91 ነጥብ 26 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ያሳያል ብለዋል።

እቅዱን ሙሉለሙሉ ለማሳካትም ምርቱ በተለያዩ የገበያ አማራጮች መውጣት፣ የህግ ማዕቀፍ አለመኖር እንዲሁም የቅመማ ቅማም ምርት ዋጋ ዝቅተኛ መሆን ዋነኛ ማነቆ መሆናቸውን አቶ በላይ ካጁዋብ አንስተዋል፡፡

ክልሉ ለማዕከላዊ ገበያ ካቀረባቸው የቅመማቅመው ምርቶች ውስጥ ኮረሪማ፣ ጥምዝ፣ በርበሬ፣ ሚጥሚጣ፣ ቁንዶ በርበሬ፣ ዝንጅብል፣ ሄል፣ ኮሰረት፣ ድንብላል፣ ሎሚናት እና የጥብስ ቅጠል(ሮዝመሪ) ይገኝበታል፡፡

ምርቶቹ እንደ አካባቢው አቅም እና የአየር ፀባይ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ይመረታል ያሉት አቶ በላይ፤ በተያዘው በጀት ዓመት 54 ሺህ 366 ቶን የቅመማቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.