የቻይና መንግስት ዜጎቹ ኢትዮጵያን እንዲጎበኟት ምክረ ሀሳብ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዓለም ላይ ተመራጭ ከሆኑ የጎብኚ መዳረሻዎች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ገለጸ።
ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ኢትዮጵያን እንዲጎበኟትም ለዜጎቹ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።
ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች መጎብኘት ይገባቸዋል ካላቸው ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ አንደኛዋ ሀገር መሆኗን በመግለጫው አንስቷል።
ሚኒስቴሩ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ቻይናውያን ሊጎበኟቸው ይገባል ያላቸውን ሀገራት ዝርዝር ያወጣ ሲሆን፥ በተለያዩ ኤጀንሲዎች አማካኝነት የጉብኝት የሙከራ መርሐ ግብር መጀመሩንም አስታውቋል።
መርሐ ግብሩ ቻይና ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን የቱሪዝም ትብብርና ተሳትፎ የበለጠ በማስፋት ረገድ አዎንታዊ ሚናው ከፍ ያለ እንደሆነምነው የገለጸው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!