Fana: At a Speed of Life!

የሌማት ትሩፋት በስርዓተ ምግብና በኢኮኖሚው ውጤት እያመጣ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር በስርዓተ ምግብና በኢኮኖሚው ላይ ውጤት እያመጣ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ ፅጌረዳ ፍቃዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፤ መርሐ-ግብሩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ በግብዓትም በውጤትም ለውጥ አምጥቷል።

ለውጤታማነቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመሰረቱ ከ20 ሺህ በላይ የማምረቻ መንደሮች አበርክቷቸው የጎላ እንደሆነም ነው ያነሱት።

በግል በርካቶች ማምረት እና መመገብ እየቻሉ መሆኑን የሚናገሩት ወ/ሮ ፅጌረዳ ፥ ለማህበራትም የስራ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።

በመሆኑም የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማቱን ለማሳደግ ንቅናቄው ዕድል ስለመፍጠሩ ነው የተናገሩት።

ስራው ከግለሰብ ጀምሮ በማህበራት እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ሃላፊዋ ፥ ሰፊ ቦታ ያላቸው ተቋማትም የማምረት ስራውን እንዲቀላቀሉ መደረጉን ገልጸዋል።

አክለውም ግንዛቤ እያደገ መምጣቱን ገልጸው ፥ ኑሮ ወድነቱን እና ገበያውን ማረጋጋት፣ ሕፃናትን ከመቀንጨር ለመታደግ የሚቻለው ምርትን በማሳደግ ብቻ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ለዚህም ሁሉም ባለው ቦታ ዶሮ ማርባት የሚያስችሉት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የጓዳ ወጪን እንዲቀንስ ጥሪ አቅርበዋል።

በማርታ ጌታቸው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.