አግሪ ፋድ እና የምግብ ማሸጊያ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ተኛው አግሪ ፋድ እና የምግብ ማሸጊያ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል።
የንግድ ትርኢቱ በግብርና፣ በምግብ ማቀነባበሪያ፣ ፕላስቲክ፣ሕትመት እና የማሸጊያ ኢንዱስትሪ ላይ ትኩረት ማድረጉ ተመላክቷል፡፡
በንግድ ትርኢቱ ከ14 አገራት የተወጣጡ ከ130 በላይ የንግድ ትርኢት አቅራቢዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ቻይና፣ ጀርመን፣ ኔዘርላንድስ፣ ሕንድ፣ ጣልያን፣ ተርኪዬ፣ ኦስትሪያ፣ ቡልጋሪያ ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ጆርዳን እና ኬንያ በንግድ ትርኢቱ የተሳተፉ የውጭ አገራት ናቸው።
የገበያ ትስስር ለመፍጠር ወቅታዊ የንግድ እድሎችን ለማወቅ እና በኢንዱስትሪው ውስጥ ስላሉ አዳዲስ ለውጦች ለማወቅ ጠቃሚ እድሎችን እንደሚፈጥርም ነው የተገለጸው።
በንግድ ትርኢቱ መክፈቻ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድን ጨምሮ አምባሳደሮች፣ የንግዱ ዘርፍ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየውን የንግድ ትርኢት ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።