Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)  ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 957 የላቦራቶሪ ምርመራ አንድ ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

ሚኒስትሯ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 123 መድረሱን በፌስቡክ ገፀቸው ላይ አስታውቀዋል።

ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ከፑንትላንድ የተመለሰና በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ 30 ዓመት የጅግጅጋ ነዋሪ ነው።

የላብራቶሪ ምርመራው የተደረገው በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በብሄራዊ የእንሰሳት ጤና በሽታዎች ምርመራ ማዕከል፣ በኢንተርናሽናል ክልኒካል ላቦራቶሪ፣ በኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በትግራይ ጤና ምርምር ተቋም፣ በአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላቦራቶሪ ነው።

በትናንትናው እለት 12 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውንም ነው ያመለከቱት።

ይህንንም ተከትሎ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ደርሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.