የኢትዮ- የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን ማስተዋወቅ አላማው ያደረገው የኢትዮ- የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ፎረም በአቡ ዳቢ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በፎረሙ የኢንቨስትመት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ለባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች እና ለዘርፉ ምቹነት የተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን እና ኮሚሽነር ለሊሴ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት አስረድተዋል፡፡
ፎረሙ የኢንቨስትመንት ከባቢውን በማነቃቃት እና ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የኢንቨትመንት ግንኙነት በማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው መግለፃቸውን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡