ዩኒሴፍ ለኮሮናቫይረስ መከላከያ የሚውል የህክምና ቁሳቁሰ ድጋፈ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በኢትዮጵያ ለኮሮናቫይረስ መከላከያ የሚውል 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቀሰ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፍ የተደረገው የህክምና ቁሳቀስ ሙሉ በሙሉ ለጤና ባለሙያዎች የሚሰጥ ሲሆን፥ የፊት መሸፈኛ ጭንብል፣ የሙቀት መለኪያ መሣሪያና የህክምና አልባሳትን የሚያካተት ነው።
የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የህክምና ቁሳቁሶቹን ለየክልሎች የሚያከፋፍል መሆኑም ተገልጿል።
ድርጅቱ ድጋፉን ያደረገው በራሱና በእንግሊዝ መንግሥት እርዳታ መሆኑ ተጠቁሟል።
በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ አዴል ኮድር ድጋፉን ለጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ማስረከባቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision