Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክና ንግድ ባንክ ለአምራች ዘርፉ የሚሰጡት ብድር እየጨመረ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአምራች ዘርፉ የሚሰጡት ብድር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ፡፡

“የፋይናንስ ተደራሽነት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ” በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው ።

በመድረኩ 3ኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አምራች ኢንዱስትሪዎች የብድር አቅርቦት በሚያገኙበት ዙሪያ ከባለድርሻዎች ጋር ምክክር እየተደረገ ነው ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአምራች ዘርፉ የሚሰጡት ብድር እየጨመረ መምጣቱም ነው በውይይቱ የተገለጸው።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷ለግሉ ዘርፍ የሚሰጠው ብድር መጨመሩ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ያሳያል።

አምራቾች ከጥሬ ዕቃ እና ከውጭ ምንዛሬ አንጻር የሚገጥማቸውን ችግር እንደሚረዱም ነው አቶ ማሞ የተናገሩት ።

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.