በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ለማድረግ ዝግጅት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች በሁሉም ማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ብቻ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ማሄ ቦዳ እንደገለጹት÷ የኤሌክትሮኒክስ የነዳጅ ግብይት ስራውን ውጤታማ ለማድረግ እንዲቻል ከሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የሙከራ ትግበራ ተጀምሯል፡፡
በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የነዳጅ ግብይት ሥርዓቱን በኤሌክትሮኒክስ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ከበደ አረጋግጠዋል፡፡
በክልሎቹ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ እንደሚከናወን መገለጹን የየክልሎቹ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮዎች መረጃ ያመላክታል፡፡
የመንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና የግል አሽከርካሪዎች ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉም ነው ኃላፊዎቹ ያሳሰቡት፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን