በመዲናዋ ነገ ምንም አይነት ሰልፍ አለመኖሩ ፖሊስ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የላብ አደር ቀንን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ምንም አይነት የአደባባይ ኩነቶችና ሰልፍ እንዲሁም ፖሊስም ሆነ የአስተዳደር አካላት የሚያውቁት ምንም ዓይነት ስብሰባ አለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ነገ ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም የላብ አደር ቀን እንደሚከበር አንስቷል፡፡
የላብ አደር ቀንን አስመልክቶም በአዲስ አበባ ከተማ ምንም አይነት የአደባባይ ኩነቶችና ሰልፍ እንዲሁም ፖሊስም ሆነ የአስተዳደር አካላት የሚያውቁት ምንም ዓይነት ስብሰባ አለመኖሩን አስታውቋል።
ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ፖሊስ ህግን የማስከበር ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያሳሰበው።
ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካል ጎን በመቆም ለፀጥታ ስራው ስኬታማነት እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርቦ÷ ህብረተሰቡ የተለመደ ቀና ትብብሩን አጠናከሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርቧል።
አዲስ አበባ ፖሊስ በፀጥታና ደህንነት ግብረ ኃይል ስም ለመላው የሀገሪቱ ላብ አደሮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ አስተላልፏል።