Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 20ኛውን ኤር ባስ 350-900 አውሮፕላን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 20ኛውን ኤር ባስ 350-900 አውሮፕላን መረከቡን አስታወቀ።

አውሮፕላኑ ዝቅተኛ የካርበን ልቀት መጠን እንዲኖረው ሆኖ የተሰራ ሲሆን፥ በማስረከቢያ በረራውም ይህን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል 30 በመቶ ቅልቅል ነዳጅ መጠቀሙ ተገልጿል፡፡

በዚህም በ2050 የካርቦን ልቀትን ዜሮ የማድረስ “ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (አይ ኤ ቲ ኤ)፣ የአሰናጅ መሣሪያ ተደራሽነት መመሪያዎች (ኤ ቲ ኤ ጂ) እና ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (አይ ሲ ኤ ኦ)” ያስቀመጡት ግብ እንዲሳካ የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ አሻራውን በማኖር አስተዋፅዖ ያደርጋል ተብሏል።

አውሮፕላኑ ወደ ኢትዮጵያ በረራውን ሲያደርግ 10 ቶን ሰብአዊ ጭነት ይዞ መምጣቱን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.