Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ሂደቶች ለሌሎች ሀገራት ዓርዓያ መሆናቸውን ማይክ ሐመር ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተከስቶ የነበረውን ጦርነት በሰላም ስምምነት የቋጨችበት መንገድ ለሌሎች ሀገራት ዓርዓያ እንደሚሆን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ገለጹ።

አሜሪካ ለሰላም ስምምነቱ መጽናት በቀጣይ የሚጠበቅባትን ድጋፍ እንደምታደርግም ልዩ መልዕክተኛው አረጋግጠዋል፡፡

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የመልሶ ግንባታ ሥራ እና የሽግግር ፍትሕ የማረጋገጥ ሂደትንም አሜሪካ እንደምትደግፍ ገልጸዋል፡፡

የፌደራል መንግሥት እና ህወሓት በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ሥር በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ስምምነት አሜሪካ በአድናቆት ትመለከተዋለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ስምምነቱ “ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ” በማበጀት ረገድ በዓርዓያነት ተጠቃሽ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

ሱዳንም ከኢትዮጵያ ልምድ በመውሰድ ጦርነት የዜጎችን ሕይወት ከመቅጠፍ ውጭ ሌላ ዓላማ እንደሌለው በመገንዘብ እና ግጭቱን በማቆም ወደ ውይይት እንድትመጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አሜሪካ ከአፍሪካ ሕብረትና ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እንዲሁም ከመሰል ተቋማት ጋር በመሆን ሱዳን ካጋጠማት ችግር እንድትወጣ ድጋፏን እንደምታደርግ ጠቁመዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.