Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶ ከ1 ሺህ አረጋዊያንና የጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር የፋሲካ በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በወላይታ ሶዶ ከ1ሺህ አቅመ ደካማ አረጋዊያንና የጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር የፋሲካ በዓል ተከበረ።

የፋሲካ በዓል ከአረጋዊያንና ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር በዚህ መልኩ መከበሩ ወገናዊ መተሳሰብ እየጎለበተ ስለመምጣቱ ማሳያ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ላለፉት በርካታ አመታት የጎዳና ህይወት ሲመሩ የነበሩ እነዚህ ዜጎች እየተደረገላቸው ባለው እገዛ ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም ከጎዳና ህይወት እንዲወጡ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የምሳ ግብዣ የተደረገላቸው አቅመ ደካማ አረጋዊያንም ጠያቂ በማግኘታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

አቅመ ደካማ አረጋዊያንና የጎዳና ተዳዳሪዎች በተደረገው የምሳ ግብዣም የሶዶ ከተማና የዞኑ አስተዳደር ትልቅ ድርሻ ነበራቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.