Fana: At a Speed of Life!

ክልሎች ለበዓሉ ፍትሐዊ ግብይት እንዲኖር እየሠራን ነው አሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች ከመጪው የፋሲካ በዓል ጋር በተያያዘ ከምርት አቅርቦት እስከ ፍትሐዊ የግብይት ሥርዓት ድረስ በትኩረት እየሠሩ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቢታ ገበያው÷ በክልሉ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ በቂ የምርት አቅርቦት መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡

ከተለያዩ ማኅበራት እና ሕጋዊ የንግድ አደረጃጀቶች ጋር ለበዓሉ አስፈላጊ አቅርቦቶችን ለማሟላት መሠራቱን ደግሞ የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሳሙኤል ሳዲሁን ተናግረዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጤ ቶሼ÷ በዓሉን ታሳቢ በማድረግ ከወትሮው የግብይት ሁኔታ በተለየ ክትትል እና ቁጥጥር እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ ለበዓል አስፈላጊ አቅርቦቶችን ለማሟላት ግብረ ኃይል በማዋቀር እና የገበያ ትስስር በመፍጠር በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

በዚህም የግብርና፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም የእንስሳት እና የእንስሳት ተዋጽኦ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓቱን በማወክ ስግብግብነት ያጠላበት ግብይት ሲያከናውኑ በነበሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ነው የሥራ ኃላፊዎች የገለጹት፡፡

የክትትል እና ቁጥጥር ሥራውን በማጠናከር ፍትሐዊ ግብይት እንዲሰፍን እየሠሩ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.