ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው ከአፍሪካ ልማት ባንክ የግብርና ዘርፍ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮሰመሪታ ሰዋሰው ከአፍሪካ ልማት ባንክ የግብርና ዘርፍ ዳይሬክተር ፓስካል ሳጊንጋ (ዶ/ር) እና ከሞሮኮ የአፈር ማዳበሪያ አምራች ድርጅት ሊቀመንበር ላህቸን ኢናህሊ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ በኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ዘርፍ ያሉ እድሎችን እና ተግዳሮቶችን በተመለከተ ለዳይሬክተሩ እና ለልዑካቸው ገለፃ አድርገዋል።
መንግስት የስንዴ ምርታማነትን ለመጨመር እና በዘረፉ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያደረጋቸውን ጥረቶች በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያን የስንዴ ፕሮጀክት መደግፍ በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡