በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የልዑካን ቡድን ለስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገባ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብቷል።
ጅቡቲ ሲደርሱም በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ልዑኩ ቀደም ብሎ በሶማሊያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረገ ሲሆን፥ በቆይታውም ከፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየቱ ይታወሳል።
በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡