በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሦስት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሦስት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት 14 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ለ247 ግለሰቦች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቅሰው፥ ከዚህ ውስጥ ሶስቱ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሶስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆናቸው ነው የተገለጸው።
ከግለሰቦቹ መካከል ሁለቱ ወንዶች ሲሆኑ፥ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ እንዳላቸው እየተጣራ መሆኑ ተመልክቷል።
አንደኛዋ የ23 ዓመት ወጣት ስትሆን በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የነበራት መሆኑም ተመላክቷል።
ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 74 ደርሷል።
በሌላ ዜና ቫይረሱ እንዳለባቸው ከተረገጠባቸው ግለሰቦች መካካል ተጨማሪ አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 14 ከፍ ብሏል።
በኢትዮጵያ እስካሁን ለ4 ሺህ 110 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision