Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀመረ።

ኢንስቲትዩቱ በቀን 96 ሰዎችን እንደሚመረምር የደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

የላቦራቶሪ አገልግሎቱ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተጀምሯል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የላቦራቶሪ ማዕከሉን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት በሃገር አቀፍ ደረጃ ቫይረሱን መመርመር የሚያስችል ላቦራቶሪ እንዲኖር መንግስት ባደረገው ጥረት ማዕከላትን የማስፋፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በሌሎች አካባቢዎችም የምርመራ ማዕከላትን በመገንባት የወረርሽኙን ስርጭት መቆጣጠር የሚያስችል ስራ ይሰራል ብለዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.