የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጸደቀ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጸደቀ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልጋት ከስምምነት በመድረስ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።
አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቅ ስላለበት ዛሬ ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባ ምክር ቤቱ የቀረበውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁን ኢቢሲ ዘግቧል።