በቅርቡ የተገኘችው አረንጓዴዋ ‘‘ጅራታም ኮከብ’’ ወደ ምድር እየተጠጋች ነው ተባለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ የተገኘችው አረንጓዴዋ ‘‘ጅራታም ኮከብ’’ ወደ ምድር እየተጠጋች መሆኑ ተሰምቷል፡፡
የስነ ፈለክ ተመራማሪዎችለተመራማሪዎች እንግዳ የሆነችው አዲሷ ‘‘ጅራታም ኮከብ’’ ወደ ምድር ያደረገችው ጉዞ 50 ሺህ ዓመታት ገደማን የፈጀ መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል፡፡
በተመራማሪዎቹ የተነሱ ፎቶግራፎች በኮከቧ አካል ዙሪያ የተለየ አረንጓዴ ቀለም እንዳለ ማየት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ሲ/2022 E3 የሰኘችው ይህቺን ኮከብ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች በባለፈው መጋቢት ወር ላይ ነው በካሊፎርኒያ ፓሎማር ኦብዘርቫቶሪ ውስጥ ያገኟት።
እንደ ዘርፉ ተመራማሪዎች ገለጻ ÷ በዛሬው ዕለት ወደ 41 ሚሊየን ኪሎ ሜትር ወይንም 26 ሚሊየን ማይል ርቀት ላይ ወደ ምድር ትቀርባለች ፡፡
ኮከቧ የዘርፉ ባለሙያዎች ኦርት ብለው ከሚጠሩት ደመና የመጣች ሲሆን ፥ በፀሐይ ስርዓት ጠርዝ ላይ ያሉ የበረዶ አካላት ስብስብ ናትም ተብሏል።
ኮከቧን ለማየትም በቀጥታ ወደ ሰሜን አቅጣጫ በመመልከት ራሷን ችላ ተለይታ ታገኟታላችሁ ያሉት የዘርፉ ምሁራን ፥ ኮከቧን ለማየት ምቹው ጊዜ ሐሙስ ጠዋት ጨረቃ ስትጠልቅ እንደሆነም ነው የገለጹት ፡፡
የኮከቦች አረንጓዴ ገጽታ መላበስ የተለመደ ነው ፤ብዙውን ጊዜ ምላሽ ሰጪ የሚባሉ የሞለኪውል ዓይነቶች ሲፈራርሱ የሚሰጠው ውጤት እንደሆነም አስረድተዋል።
መሰል ቀለማትን የያዙ ኮከቦች ቀለማትን በደማቁ በሚያሳዩ ዲጂታል ካሜራዎች ቢነሱ ተመራጭ እንደሆነም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡