ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በኮቪድ-19 ሕይወታቸው ላለፈው ሁለት ኢትዮጵያውያን ሀዘናቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 27፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በኮቪድ-19 ሕይወጣቸው ላለፈው ሁለት ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ለሁለቱም በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ከልብ መጽናናትን፥ ለነፍሳቸው ዘላለማዊ እረፍትን እንዲያገኙ ተመኝተዋል።
“ዜናውን የሰማችሁ ሁሉ እንድትረጋጉ እና የወጡትን መመሪያዎች በጥብቅ እንድትከተሉ አሳስባለሁም” ነው ያሉት።
“የሚገጥመንን ሁኔታ በጋራ ለማስተናገድ በምንዘጋጅበት በዚህ ጊዜ፣ በእምነት ጸንተን ቫይረሱ በማኅበረሰባችን መካከል እንዳይሠራጭ በትጋት ልንሠራ ያስፈልጋልም” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ “አካላዊ ርቀታችሁን ጠብቁ፣ እጆቻችሁን በሚገባ ታጠቡ፣በምትችሉት መንገድ ሁሉ ለሌሎች ድጋፍ አድርጉ” ሲሉም አሳስበዋል።