Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፀሐይ ሽፈራው እንዲሁም የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ተቋማት የተፈራረሙት ስምምነት በቴክኖሎጂ የታገዘ የባንክ መረጃ አሰባሰብና አያያዝ እንዲኖር የሚያግዝ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን የሚያዘምን መሆኑም ተጠቁሟል።

የባንኩ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ፀሐይ ሽፋራው ÷ ስምምነቱ ባንኩ የአገልግሎት አሠጣጡን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምቹና ቀልጣፋ የማድረግ ሥራን የበለጠ ለማሳደግ ያስችላል ብለዋል።

ባንኩና ኢንስቲትዩቱ በሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ የባንኪንግ አፕልኬሽን ዘርፍ ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ የባንኩን አገልግሎት ለማዘመን የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ሥራዎችን በጋራ እንደሚሠሩም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው ÷ ስምምነቱ ባንኩ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ እየተወጣ ያለውን ሥራ ይበልጥ ለመደገፍ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ዘርፎችን በማዘመን ረገድ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው የተገባው ስምምነት የፋይናስ ሥርዓትን በማዘመን ረገድ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል።

በቤተልሔም መኳንንት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.