Fana: At a Speed of Life!

በ1 ቢሊየን ብር ካፒታል በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ተመረቀ

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ዶክተር ይልቃል ባደረጉት ንግግር÷ የአማራ ክልል መንግሥት ለፋብሪካ ባለቤቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው “ዜማ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ” ለ300 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩ እና 3 ሺህ ሰዎች ደግሞ በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡

ከምረቃ ሥነ ስርዓቱ በኋላ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና ባለሃቶች÷ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የአቶ በላይነህ ክንዴን የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካም ጎብኝተዋል፡፡

በዘላለም ገበየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.