Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የዓለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ በአውሮፖ እና የአሜሪካ ዋና አስተባባሪና የኢስላሚክ ሊግ የዋና ፀሐፊው አማካሪ ዶክተር አብዱልአዚዝ ሳርሃን ልዑካቸውን በመምራት በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በውይይቱ የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ በቀጣይ በኢትዮጵያ ሊሰራቸው ባቀዳቸው ሁሉ አቀፍ የሰላም፣ የልማት፣ የጤና እና የትምህርት እቅዶች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል፡፡

አቶ ደመቀ÷ የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ በኢትዮጵያ ሊሰራቸው ላሰበው የልማት ስራዎች ሁሉ የሚፈለገውን ድጋፍ እና እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የዓለም አቀፍ ሙስሊሞች ሊግ ልዑካን በዛሬው ዕለት ከሌሎች መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደረግ ከኢትዮጵያ እስልማና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.