የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሞሮኮ የሚያደርገውን ጉዞ ጀምሯል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ውድድር ዝግጅት ወደ ሞሮኮ የሚያደርገውን ጉዞ ጀምሯል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ወደ ግብፅ ካይሮ በረራ ያደረገ ሲሆን ፥ ቡድኑ ከደቂቃዎች በፊት በሰላም ካይሮ መድረሱ ታውቋል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ለትንሽ ደቂቃዎች በካይሮ አየር ማረፍያ ቆይታ ካደረገ በኋላም ወደ ሞሮኮ ጉዞውን የሚቀጥል መሆኑን ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡