በሐረሪ ክልል ባለፉት 5 ወራት 640 ሚሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 7፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ባለፉት አምስት ወራት 640 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ሀላፊ አቶ በቀለ ተመስገን ÷ክልሉ በበጀት ዓመቱ አምስት ወራት 627 ሚሊየን ብር ለመሰብስብ አቅዶ 640 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገልፀዋል፡፡
በዚህም 346 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ከቀጥታ ታክስ፣ 187 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ 40 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም 66 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የተሰበሰበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ገቢው ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ142 ነጥብ 60 ሚሊየን ብር ብልጫ ወይም የ28 ነጥብ 7 በመቶ እድገት ማሳየቱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም በበጀት አመቱ ለመሰብሰብ የታቀደውን 1 ነጥብ 36 ቢሊየን ብር ገቢ ለማሳካት ይሰራል ነው ያሉት፡፡