የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ለይቶ ማቆያ ሊገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለይቶ ማቆያ ሊገቡ መሆኑ ተነገረ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ ረዳት በኮሮና ቫይረስ መያዙን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት ራሳቸውን ለይተው እንደሚገኙ ተነግሯል።
ኔታንያሁ ከቅርብ አማካሪዎቻቸው ጋር በመሆን ለይቶ ማቆያ እንደሚገቡም ነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ያስታወቀው።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች አማካሪ በዛሬው ዕለት በቫይረሱ እንደተያዙ መረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision