የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንና የልማት አጋሮች የጋራ ምክክር ተካሄደ
አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንና የልማት አጋሮች 2ኛው የጋራ ምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄዷል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በመድረኩ ፥ በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት እና በገንዘብ ሚኒስቴር ስምምነት የተመሰረተው ትረስት ፈንድ ለኮሚሽኑ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰመሪታ ሰዋሰው÷ ከአለም አቀፍ የልማት አጋሮች የሚገኘው የገንዘብ ድጋፍ ትረስት ፈንድ ተቋቁሞ በተባባሩት መንግስታት የልማት ድርጅት እንዲተዳዳር መደረጉ ኮሚሽኑ ያለማንም ጣልቃ ገብነት ተልእኮውን እንዲወጣ ያስችለዋል ብለዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ሀላፊ አቺም ስቴይነር በበኩላቸው ÷ባለፉት አምስት ወራት 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ለኮሚሽኑ ወጪ ተደርጎ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ኮሚሽኑ ተልእኮውን እንዲወጣ ትረስት ፈንዱ የበኩሉን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃላፊው መግለፃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡