ለሁሉም ሕጻናት ምቹ ኢትዮጵያን ለመፍጠር መሥራት ይገባል – ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለነገ ሀገር ተረካቢ ሕጻናት ልዩ ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ለሁሉም ሕጻናት ምቹ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በትኩረት መሥራት ይገባል ሲሉ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናገሩ፡፡
የዓለም የሕጻናት ቀን በዓለም ለ33ኛ በኢትዮጵያ ለ17ኛ ጊዜ÷ “ምቹና ሰላማዊት ኢትዮጵያ ለሁሉም ሕጻናት” በሚል መሪ ሐሳብ በሚዛን አማን ከተማ ተከብሯል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ለሁሉም ሕጻናት ምቹ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡
የሕጻናትን መብት ማክበርና በሥነምግባር አንጾ ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በአብዱ ሙሐመድ