አንጋፋው አርቲስት ዓሊ ቢራ ዘመን ተሻጋሪ የጥበብ አሻራ ትቶልን አልፏል – ከንቲባ ከድር ጁሃር
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው አርቲስት ዓሊ ቢራ ዘመን ተሻጋሪ የጥበብ አሻራ ትቶልን አልፏል ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ተናገሩ፡፡
የአርቲስት አሊ ቢራ የአስክሬን የሽኝት መርሐ- ግብር በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሐ- ግብሩ የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ÷ አንጋፋው አርቲስት ዓሊ ቢራ እንደተወደደና እንደተከበረ ከከፍታው ሳይወርድ እስከመጨረሻ መጓዝ የቻለ ነው ብለዋል፡፡
አንጋፋው አርቲስት ዓሊ ቢራ ዘመን ተሻጋሪ የጥበብ አሻራ ትቶልን አልፏል፤ የድሬዳዋ ፈርጥና ህያው ምልክት ሆኖ ኖሯልም ሲሉ ነው የገለፁት፡፡
አርቲስቱ ለህዝብ ነፃነትና መብት መከበር ዕድሜ ልኩን በሥራዎቹ ታግሏል ያሉት ከንቲባው ÷ በዚህም በጎ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለ የህዝብ ልጅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዘመን ተሻጋሪ የጥበብ አሻራ ትቶልን አልፏል ሲሉም የአስተዳደሩ ከንቲባ ተናግረዋል፡፡
በፌቨን ቢሻው