ጥቅምት 24 በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ እንደሚውል መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት የፈፀመበት ጥቅምት 24 ሁለተኛ ዓመት በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ በኩል በተለያየ ዝግጅት ታስቦ እንደሚውል የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ገልፀዋል።
አሸባሪ ቡድኑ ሀገር የማፍረስ ዓላማን በማንገብ ሰራዊቱ ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙን አስታውሰዋል።
ቡድኑ በዚህ ተግባሩ ፀረ ህዝብና ፀረ ሀገር መሆኑን ያሳየበት ነው ሲሉም ጥቅም 24 በልዩ ሁኔታ በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ እንዲሁም ሰራዊቱ ባለበት ቦታ ታስቦ እንደሚውል ነው የገለጹት።
የበዓሉ መከበርም ቂምና ጥላቻን ለመግለጽ ሳይሆን ይህ የክህደት ተግባር ዳግም እንዳይፈጸም ጭምር ለማስተማር እና ለማስገንዘብ መሆኑን አስረድተዋል።
በታሪኩ ለገሰ